የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ ባጭሩ፤

ኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ በግለሰቦች አነሳሽነት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1987 ጀምሮ ይንቀሳቀስ ነበር፡፡ ከ1998 ጀምሮ ግን በኖርዌይ ውስጥ እንደ ድርጅት ሆኖ ተመዝግቦና እውቅና አግኝቶ ይንቀሳቀሳል፡፡ ማህበሩ በየሁለት አመቱ ዲሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ ተወካዮች ይመርጣል፡፡ እንዚህም ተወካዮች ለሁለት አመታት ያክል ማህበሩን ይመራሉ፡፡

amh-category: 

የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ ይጠቅማል!


ኢ.ማ.ኖ. አንደኛውና ዋናው እቅዱ ኖርዌይ ውስጥ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መካከል ስምምነትና ውህደትን የበለጠ ለማዳበር ነው፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ ትምህርታዊ እንቅስቃሴወችና ውይይቶች ይደረጋሉ፡፡ እርስዎም የማህበሩ ባለቤትነት እንዲሰማዎት ኢ.ማ.ኖ የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል፡፡

amh-category: 

የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይና በዓላት


ኢማኖ አድስ ዓመት፣ ገና በዓል እና ፋሲካን ከኢትዮጵያውያን ጋር ያከብራል፡፡ ኢድ አልፈጥርና አረፋንም ማህበሩ በአውሮፓውያን 2011 ላይ ማክበር ጀምሯል፡፡ እነዚህ በዓላትን ስናከብር ልክ እንደ ኢትዮጵያ ውስጥ በዕለቱ ቀን ባይሆንም ቀራቢው ቅዳሜ ላይ እናከብራለን፡፡ በርግጥ ግለሰቦችና የሀይማኖት ተቋማት በዕለቱ ላይ እንደሚያከብሩ አይዘነጋም፡፡

amh-category: