Image Image Image
✍ በቅርብ የገባ
ማህበሩ እና ለቅዳሜ ቦታ

ኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ ቅዳሜ ቅዳሜ ላይ ዝግጅት ካለ ማህበረሰቡ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እንዲያደርግ ሎካል አግኝቷል። በአውሮፓውያን አፕሪል 27.2024 ላይ ጀምሯል። በዚሁ አጋጣሚ በጋሼ አበራ የተጻፈው "የዓለማችን ምስጢራት" መጽሃፍ ዙሪያ ውይይትና አስተያየት ተደርጓል።

ተጨማሪ

ይዘት ➞ መነሻ ➞ አላማ ➞ ማህበሩ እና በአላት ➞ መተዳደሪያ ደንብ ➞ ጥሩ ስራ ይፈልጋሉ? ➞ ድንቅ ፎቶዎች ➞ አባል ይሁኑ
✍ አድራሻ ethionor1@gmail.com
+47 97002935
Orgnr. 984047355
☝ አመታዊ ክፍያ ባንክ፤ 05401729420
ቪፕስ፤ 500424
ለአዋቂ፤ ከ200 ጀምሮ
ለህጻናት፤ 80 ክሮነር
ክፍያውን ሲፈጽሙ "medlemskontingent" የሚለውን መልዕክት ያካቱበት።
በቅድሚያ እናመሰግናለን!

እንኳን ደህና መጡ!

ecn defin ethiopia norway amharic ethiopian community

ኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ በግለሰቦች ተነሳሽነት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1987 ጀምሮ ይንቀሳቀስ ነበር፡፡ ከ1998 ጀምሮ ግን በኖርዌይ ውስጥ እንደ ድርጅት ሆኖ ተመዝግቦና እውቅና አግኝቶ ይንቀሳቀሳል፡፡ ማህበሩ በየ ሶስት አመቱ ዲሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ ተወካዮች ይመርጣል፡፡ እንዚህም ተወካዮች ሶስት አመታት ያህል ማህበሩን ይመራሉ፡፡

የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ ሰላምንና ዴሞክራሲን ለሚሹ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆችን ለማስተናገድ ምንጊዜም ክፍት ነው፡፡ ወደፊትም በዚሁ መልክ ይቀጥላል፡፡ ማህበራችን ማንንም በዘር ወይም በሃይማኖት አይለይም፡፡ ስለዚህ ኢ.ማ.ኖ. የሁሉንም ኢትዮጵያውያንን ፍላጎት ለማሟላት የግለሰብ ነጻነትን ያስቀድማል፡፡

ህበሩ ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኢትዮጵያውያን እንድሁም ስለኖርዌይና ኖርዌጅያውያን ቀና አስተሳሰብና ግንዛቤ አለው፡፡ ማህበሩ በኖርዌይ ውስጥ ተሰሚነት ኖሮት ተጽዕኖ እንዲያደርግ ኢትዮጵያውያን በሰፊው የማህበሩ ተሳታፊና አባል እንደሚሆኑ ማህበሩ በኢትዮጵያውያን ላይ ይተማመናል፡፡ የማህበሩ አንደኛውና ዋናው አላማ በኢትዮጵያውያን መካከል ስምምነትና ውህደትን የበለጠ ለማዳበር ነው፡፡ ከዚህም በማያያዝ የተለያዩ ትምህርታዊ እንቅስቃሴወችና ውይይቶች ለማድረግ እቅድ ያወጣል፡፡ ለምሳሌ፤ የኖርዌይን ባህልና ወግ እንልመድ፣ የራሳችንንም አንርሳ፣ ስለ ሙያና ስራ ማግኘት፣ ስለ ቀጠሮና ምንነት በመሳሰሉት ላይ ትምህርታዊ ውይይት ለማድረግ እቅድ ያወጣል፡፡

ማህበራችን እንዲሻሻል አንዳንድ ምቹና ምክንያታዊ ለውጦች እናደርጋለን፡፡ አዝናኝና ትምህርታዊ ምሽቶችም ይኖሩናል፡፡ ይህንን በተመለከተ ማስታወቂያዎች ቀደም ብለን እንለጥፋለን፡፡ ይኸን አላማ ለማሳካት ለማሳካት ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች እንደሚተባበሩን እንተማመናለን፡፡

ማህበሩ መቼ ተመሰረተ?

➟ በግለሰቦች ተነሳሽነት ሃሳብ መነጨ።
➟ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1987 ላይ መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡
➟ 1998 ላይ በኖርዌይ ውስጥ ማህበር ሆኖ ተመዘገበ፡፡
➟ Orgnr. 984 047 355
➟ DEN ETIOPISKE FORENINGEN I NORGE

ለምን ተመሰረተ?

➟ ወድማማችነትና እህታማማችነት ለማጎልበት፤
➟ ኖርዌጃውያንና ሌሎች ዜጎች ጋር ወዳጅነት ለመፍጠር፤
➟ የኖርዌይን ባህልና አኗኗር ለማላመድ መረጃ ለመስጠት፤
➟ የኢትዮጵያን ታሪክ፣ ወግና፣ ባህል ለሌሎች ለማስተዋወቅ፤
➟ የኢትዮጵያውያንን በዓላት በጋራ ለማክበር፤

እንዴት መተባበር ይችላሉ?

➟ መደበኛ አባል በመሆን፤
➟ ትምህርታዊና በዓላዊ ዝግጅቶች ላይ በመገኘት፤
➟ ስብሰባ ላይ የውሳኔ ተካፋይ በመሆን፤
➟ ምን ላግዝ ብሎ ማህበሩን በመጠየቅ፤
➟ ከተመረጡ አመራር ውስጥ በመግባት፤
➟ ማህበሩን በማስተዋወቅ፤
➟ ገንቢ ሃሳብ በመስጠት፤

ከታች አስተያየት ወይም ነጥብ ይስጡ!

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
1000
Powered by Commentics

የተሰጡ አስተያየቶች

አስተያየት ገና አልተሰጠበትም። የመጀመሪያው ይሁኑ!