የ2023 አባልነት ክፍያዎን በባንክ ወይም በቪፕስ እንዲያስገቡልን በትህትና እንጠይቃለን።
ባንክ፤ 05401729420
ቪፕስ፤ 500424
የዓመታዊ ክፍያ መጠን፤
ለአዋቂ፤ ከ200 ክሮነር አንስቶ
ለህጻናት፤ 80 ክሮነር።
ክፍያውን ሲፈጽሙ "medlemskontingent" የሚለውን መልዕክት ያካቱበት።
የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ ባጭሩ፤

የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ በግለሰቦች ተነሳሽነት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1987 ጀምሮ ይንቀሳቀስ ነበር፡፡ ከ1998 ጀምሮ ግን በኖርዌይ ውስጥ እንደ ድርጅት ሆኖ ተመዝግቦና እውቅና አግኝቶ ይንቀሳቀሳል፡፡ ማህበሩ በየ ሶስት አመቱ ዲሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ ተወካዮች ይመርጣል፡፡ እንዚህም ተወካዮች ሶስት አመታት ያህል ማህበሩን ይመራሉ፡፡
የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ ሰላምንና ዴሞክራሲን ለሚሹ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆችን ለማስተናገድ ምንጊዜም ክፍት ነው፡፡ ወደፊትም በዚሁ መልክ ይቀጥላል፡፡ ማህበራችን ማንንም በዘር ወይም በሃይማኖት አይለይም፡፡ ስለዚህ ኢ.ማ.ኖ. የሁሉንም ኢትዮጵያውያንን ፍላጎት ለማሟላት የግለሰብ ነጻነትን ያስቀድማል፡፡
ኢ.ማ.ኖ. ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኢትዮጵያውያን እንድሁም ስለኖርዌይና ኖርዌጅያውያን ቀና አስተሳሰብና ግንዛቤ አለው፡፡ ማህበሩ በኖርዌይ ውስጥ ተሰሚነት ኖሮት ተጽዕኖ እንዲያደርግ ኢትዮጵያውያን በሰፊው የማህበሩ ተሳታፊና አባል እንደሚሆኑ ማህበሩ በኢትዮጵያውያን ላይ ይተማመናል፡፡ የማህበሩ አንደኛውና ዋናው አላማ በኢትዮጵያውያን መካከል ስምምነትና ውህደትን የበለጠ ለማዳበር ነው፡፡ ከዚህም በማያያዝ የተለያዩ ትምህርታዊ እንቅስቃሴወችና ውይይቶች ለማድረግ እቅድ ያወጣል፡፡ ለምሳሌ፤ የኖርዌይን ባህልና ወግ እንልመድ፣ የራሳችንንም አንርሳ፣ ስለ ሙያና ስራ ማግኘት፣ ስለ ቀጠሮና ምንነት በመሳሰሉት ላይ ትምህርታዊ ውይይት ለማድረግ እቅድ ያወጣል፡፡
ማህበራችን እንዲሻሻል አንዳንድ ምቹና ምክንያታዊ ለውጦች እናደርጋለን፡፡ አዝናኝና ትምህርታዊ ምሽቶችም ይኖሩናል፡፡ ይህንን በተመለከተ ማስታወቂያዎች ቀደም ብለን እንለጥፋለን፡፡ ይኸን አላማ ለማሳካት ለማሳካት ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች እንደሚተባበሩን እንተማመናለን፡፡
Add new comment