የ2023 አባልነት ክፍያዎን በባንክ ወይም በቪፕስ እንዲያስገቡልን በትህትና እንጠይቃለን።
ባንክ፤ 05401729420
ቪፕስ፤ 500424
የዓመታዊ ክፍያ መጠን፤
ለአዋቂ፤ ከ200 ክሮነር አንስቶ
ለህጻናት፤ 80 ክሮነር።
ክፍያውን ሲፈጽሙ "medlemskontingent" የሚለውን መልዕክት ያካቱበት።
ስለ ማህበሩ መረበ-ገጽ አስተያየት አለዎት?

የማሻሻያ ሃሳብ፣ ምክር ወይም የሚጨመር ሌላ ጠቃሚ ነገር አለኝ ካሉ ሃሳብወን ከታች ባለው የሃሳብ መስጫ ቦታ ላይ ይጻፉት፡፡
ወይም ሌላ በልብዎ ውስጥ ለማህበራችን ይጠቅማል ብለው ያሰቡትን ከመጻፍ ወደ ኋላ አይበሉ፡፡
ማህበሩ በቅድሚያ ያመሰግናል፡፡
የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይና በዓላት አከባበር፤

ማህበሩ አድስ ዓመት፣ ገና በዓል እና ፋሲካን ከኢትዮጵያውያን ጋር ያከብራል፡፡ ኢድ አልፈጥርና አረፋንም ማህበሩ በአውሮፓውያን 2011 ላይ ማክበር ጀምሯል፡፡
የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ ይጠቅማል!

የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ አንደኛውና ዋናው እቅዱ ኖርዌይ ውስጥ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መካከል ስምምነትና ውህደትን የበለጠ ለማዳበር ነው፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ ትምህርታዊ እንቅስቃሴወችና ውይይቶች ይደረጋሉ፡፡
የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ ባጭሩ፤

የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ በግለሰቦች ተነሳሽነት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1987 ጀምሮ ይንቀሳቀስ ነበር፡፡ ከ1998 ጀምሮ ግን በኖርዌይ ውስጥ እንደ ድርጅት ሆኖ ተመዝግቦና እውቅና አግኝቶ ይንቀሳቀሳል፡፡
የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌ መተዳደሪያ ደንብ

የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌ መተዳደሪያ ደንብ
የማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ ከታች በጂዲኤፍ ተያይዞ ቀርቧል፡፡ ይኸን መተዳደሪያ ደንብ በማሰናዳትና በማርቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ ኢትዮጵያውያን ማህበሩ ያመሰግናል፡፡
ኢትዮጵያውያን በስደት በሚኖሩበት በኖርዌይ የሚያጋጥሟቸውን የኑሮ ውጣ ውረድ ሁሉ በጋራ አሸንፈው፤ አዲስ ከተቀላቀሉት ሕብረተሰብ ወግና ባህል ጋር ተዋህደውና ...........
እንዲሁም ከሀገራቸው ከኢትዮጵያ ባህላዊ ቅርሶችና እሴቶች ጋር ያላቸው ቁርኝትና ትስስር፤ ከሕዝቧ እጣፋንታ ጋር ያላቸው መስተጋብር ተጠናክሮ ...........