የ2023 አባልነት ክፍያዎን በባንክ ወይም በቪፕስ እንዲያስገቡልን በትህትና እንጠይቃለን።
ባንክ፤ 05401729420
ቪፕስ፤ 500424
የዓመታዊ ክፍያ መጠን፤
ለአዋቂ፤ ከ200 ክሮነር አንስቶ
ለህጻናት፤ 80 ክሮነር።
ክፍያውን ሲፈጽሙ "medlemskontingent" የሚለውን መልዕክት ያካቱበት።
የሚወዱትንና የሚያልሙትን ስራ ለማግኘት የስራ አፈላለግ ስልት!

ማንም ሰው ቢሆን የሚፈልገውንና ያለመውን ስራ ማግኘት ይወዳል። ምክንያቱም ጥሩና ተስማሚ ሥራ ማግኘት ለደመወዝ ብቻ ሳይሆን በራሱ በስራው እርካታ ለማግኘትና እድገት ለመጨመር ነው። ገና ሲጀመር ሥራ የማግኘቱን ክፍል ስኬታማ ለማድረግ ደግሞ እራሱን የቻለ አካሄድና ስልት አለው። ይህ የሥራ አፈላለግ ስልት ውጭ በምንገኝ ኢትዮጵያዊያን ላይ ያተኮረ ቢሆንም የትም አገር ቢሆን ለማንኛውም ዜጋ ሊጠቅም ይችላል። ምናልባት በማደግ ላይ ያሉ አገሮች ይህንን የሥራ አሰጣጥና አፈላለግ ስልት ሙሉ በሙሉ ላይጠቀሙበት ይችላሉ። ባደጉ አገሮች ውስጥ ግን ስልቱ የተለመደ ነው፡፡
ስለዚህ ማንኛውም ዜጋ አገሩ ውስጥም ሆነ ሌላ አገር ቢኖርም፤ እዚህ ጽሁፍ ላይ የተጠቀሰውን የሥራ አፈላለግ ደንብና ስርአት ቢያውቅ ይጠቅመዋል ብዬ አስባለሁ፡፡ እርስዎ ይህንን ስልት በትክክል ከተጠቀሙበት ከአንድ ስራ በላይም ሊያገኙ ስልሚችሉ ስራ መምረጥ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ እኔ ባንድ ወቅት ላይ ሁለት ሥራዎች አግኝቼ አንዱን የተሻለውን ልመርጥ ችያለሁ፡፡ ስራ ሲመርጡ ግን ወዳጅና ዘመድ ማማከር ምርጫውን ቀላል ያደርገዋል፡፡
ይህ ሊሆን የቻለው ሌላ ሥራ ላይ እያለሁ ቢሆንም ሶስት ዓመታት ሙሉ የተሻለ ሥራ ፍለጋ ላይ ነበርኩ። በዚህ ጊዜ ውስጥ የተለያየ ትምህርት ወስጃለሁ፤ ስህተቶችም ሰርቻለሁ፡፡ የመጀመሪያም ሆነ የተሻለ ሥራ ለማግኘት ቋሚ የሆነ ህግና ደንብ ወይም የስራ አፈላለግ ህግ የለም፡፡ እንደ ሁኔታው ይለያያል፡፡ መሰረታዊ አካሄዱ ግን ይመሳሰላል፡፡ በግሌ የማውቀውንና የወሰድኩትን ልምድ ለሌሎች ባካፍል ግን በጣም ደስ ይለኛል፡፡
እዚህ የኢትዮጵያ ማህበር በኖርዌ ዌብ ጣቢያ ላይ የቀረቡት የስራ አፈላለግ ስልቶች በደንብ ተነበው በትክክል ከተፈፀሙ አንድ ስራ ማግኘት ቀርቶ ስራ ለመምረጥም ጭምር እድል ያሰፋሉ፡፡ እነዚህ ስልቶች የተጻፉት ባንድ ንጋት ምርምር አይደለም፡፡ ውጤትም ለማግኘት ከፈለጉ በስልቶቹ መሰረት ልምምድ፣ ክትትልና ትኩረት ማድረግ አለብዎት፡፡ ስልቱን በቅደም ተከተል አንብበውና ተረድተው በተግባር ከተረጎሙት ስራ የማግኘቱ ዕድል ይሰፋልዎታል! በሦስት አመታት ጊዜ ውስጥ ከመቶ በላይ ማመልከቻዎች ልኬ ወደ በርካታ ቃለ ምልልሶች ተጠርቼ ነበር፡፡ በደንብ እየታሸሁኝና እየበሸቅሁ ስህተትም ሆነ ትምህርት ወስጃለሁ፡፡ ስለዚህ እርስዎ ስልቱን በተገቢው ካዎቁት ልክ እንደኔ ማንም ወገኛ ስራ ቀጥሪ በነገር አያሸዎትም!!! ስልቱንም ለማወቅ ሶስት አመት መጠበቅ የለበዎትም፡፡ አሁን አንድ ገጽ ላይ እያነበቡት ነው፡፡ ልምምድ ግን ይፈልጋል፡፡ አሁን ኮተት አታብዛብኝ፥ ወደ ቁም ነገሩ እንግባ አይሉኝም አንዴ…? እሺ በቃ…
ፋንታው ተሰማ
ለ ኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ፡፡
Add new comment