የ2023 አባልነት ክፍያዎን በባንክ ወይም በቪፕስ እንዲያስገቡልን በትህትና እንጠይቃለን።
ባንክ፤ 05401729420
ቪፕስ፤ 500424
የዓመታዊ ክፍያ መጠን፤
ለአዋቂ፤ ከ200 ክሮነር አንስቶ
ለህጻናት፤ 80 ክሮነር።
ክፍያውን ሲፈጽሙ "medlemskontingent" የሚለውን መልዕክት ያካቱበት።
የስራ ማመልከቻ አጻጻፍ፣ ሂደቱና ክትትሉ፤
የስራ ማመልከቻ አጻጻፍ፣ ሂደቱና ክትትሉ፤

ስራ ማመልከቻ የአመልካቹን ማንነት የሚገልጽ ነው፡፡ ስለዚህ ማመልካቻው ሲጻፍ ተገቢ ጥንቃቄና ትኩረት ያስፈልገዋል፡፡ ኮተትም ሳይበዛበት አጠር ብሎ ግልፅና ለመረዳት ቀላል መሆን አለበት፡፡ ቀጣሪዎች ብዙ ማመልከቻዎች ስለሚደርሷቸው እጥር ምጥን ያሉ ማመልከቻዎችን ሊመርጡ ይችላሉ፡፡ እንግዲህ ማመልከቻ ሲፅፉ ቀን፣ የእርስዎ ሙሉ ስምና አድራሻ ይቀድማል፡፡ ከዚያም የስራው አይነት ከነ አርእስቱ ጎላ ብሎ በአርእስት መልክ ገባ ብሎ ይሰፍራል፡፡ ወደ ዝርዝር ከመግባትዎ በፊት ስራውን በተመለከተ መቼና ከማን ጋር በስልክ ጥሩ ውይይት እንደነበረዎት ቢጠቅሱ ይታዎሳሉ፡፡ ከዚያም ይኸን ስራ ለምንና እንዴት እንደፈለጉት ባጭሩና በዝርዝር ያቀርባሉ፡፡ የትምህርት ጊዜ፣ የስራ ልምድ፣ በትርፍ ጊዜ የሚደረጉ የተለያዩ ዝንባሌዎች፣ ወዘተ እራሱን በቻለ ገጽ ላይ እጥር ምጥን አድርጎ ማቅረብ የተለመደ ነው፡፡
በተጨማሪም አመልካቹ ባሁኑ ጊዜ ምን እንደሚያደርግና ህይወቱም ምን እንደሚመስል በገንቢ መልክና ባጭሩ ቢያቀርብ ማመልከቻውን ሁለገብ ያደርገዋል፡፡ አመልካቹ በራሱ አስፈላጊና ጠቃሚ ናቸው ብሎ ያመነባቸውን የራሱን ሁኔታዎችና ልዮ ችሎታዎች ቢጠቅስ ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም፡፡ በመጨረሻም እርስዎን የሚያዉቁዎትንና የጠየቋቸውን የሁለት ወይም ሶስት ተጠሪ ግለሰቦች ስም ከነሙያቸው ያሰፍራሉ፡፡ የተጠሪዎቹን ስም ለቃለ ምልልስ ሲቀርቡም ማሳወቅ ይችላሉ፡፡ ይኸን እንደ ምርጫዎና እንደ ስራው ማስታወቂያ አይነትና ፍላጎት ይለያያል፡፡ ተጠሪዎቹም ድንገት ተደውሎላቸው እንዳይደናገሩ ጉዳዩን በቅድሚያ ይንገሯቸው፤ ያስታውሷቸውም፡፡
ማመልከቻውም ከተላከ ከሶስት እስከ አምስት ቀናት በኋላ ከዚህ በፊት ያነጋገሩት ሰው ደግሞ መደወል ጥሩ ነው፡፡ ስልኩንም እራሱ ሰውዬው ካነሳው/ችው በስም “ ሰላም እከሌ” ብሎ ንግግር መጀመር ነው፡፡ ለምሳሌ “በዚህ ቀን ላይ ስለዚህ ስራ ተነጋግረን ነበር፡፡ ማመልከቻ ልኬአለሁ፡፡ ስለ ማመልከቻው ምን ይመስልዎታል? ሌላ ተጨማሪ ነገር የምትፈልጉት ካለ እልካለሁ፡፡” ብሎ መጠየቅ ይጠቅማል፡፡ ማመልከቻው እስከዛሬ ድረስ ያልተነበበ ከሆነ አርስዎ ስለደወሉ ማመልከቻው ከተቀመጠበት ተነስቶ ወይም ተመዞ አሁን ሊነበብ ይችላል።
ዋናው ቁም ነገር ግን አርስዎ አሁን እራስዎን እንደገና ለሁለተኛ ጊዜ አስተዋወቁ፡፡ የራስዎንም ማመልከቻ በደንብ እየተከታተሉ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ያነጋገሩትን ሰው በስም አስታወሱ፡፡ ይህንንም ስራ ለማግኘት ፍላጎትዎን እንደገና አሳዩ፡፡ ማመልካቻውም ከንብብሩ ላይ ተነስቶ ወይም ተመዞ ታየለዎት፡፡ ቀጣሪውም አርስዎን በቀላሉ ያስታውሰዎታል፡፡
ንግግሩም በሚካሄድበት ጊዜ እርስዎ እንደ ስራ ለማኝ ወይም ተስፋ ቢስ አይነት ሆነው መቅረብ የለብዎትም፡፡ ባነጋገር ሁኔታና በድምፅ ቃና በራስዎ የሚተማመኑ መሆንዎን ማሳወቅ መቻል አለብዎት፡፡ ይህ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ላልተጠበቁ ጥያቄዎችና መልሶች በስልክም ቢሆን ቅሉ ዝግጁ መሆንና በተቻለ መጠን ምክንያታዊ ጥያቄ ማቅረብና መልስም መስጠት ከቀጣሪው ነጥብ ያሰጣል፡፡ መጨረሻ ላይም አመስግኖ ለቃለ ምልልስ እንድምጠራ ተስፋ አደርጋለሁ ሳይሆን ለቃለ ምልልስ እንደምጠራ እጠብቃለሁ ብለው በጨዋነት የስልኩን ንግግር መደምደም ነው፡፡ ዘንድሮ እኮ በጣም ደፋርና አይን አውጣ ሆንኩኝ ብለው አይስጉ። እንደ ሞኝ ሆነው ካልቀረቡ በስተቀር እስካሁን ድረስ ማመልከቻዎን በትክክል እየተከታተሉ ነው፡፡
ዋናው ነገር ወሬ ሳያበዙ ባጭሩ መጠየቅ፣ መልስ መስጠትና በጊዜው ውይይትዎን መጨረስ ነው።
በሚቀጥሉት ቀናት ወይም ሳምንታት ውስጥ ለቃለ ምልልስ ካልተጠሩ ከላይ በተጠቀሰው መልኩ ሌላ ስራ ለማግኘት አደናውን መቀጠል ነው፡፡ ለቃለ ምልልስ ከተጠሩ ደግሞ እሰየው ነው፡፡ አንድ እርምጃ ወደፊት፡፡ አሁን ደግሞ ይህንን ስራ ለማግኘት ምን መደረግ እንዳለበት አብረን እናያለን፡፡
ለማስታወስ ያህል የመጀመሪያው የስራ አፈላለግ ስልት ላይ በዝርዝር የሚከተሉትን ነጥቦች አይተናል፤
ለስራ ፍለጋ ቅድሚያ ዝግጅት፣
ክፍት የስራ ቦታዎች ምን ላይና እንዴት እንደሚዎጡ፣
ማመልካቻ ከመጻፉ በፊት ስለሚደርጉ ቅድመ ዝግጂቶችና፣
የማመልከቻ አጻጻፍና ክትትሉን አይተናል፡፡
ፋንታው ተሰማ
ለ ኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ፡፡
አስተያየት ይስጡ፤
english language & literature
your invitation for as to aplay as here is good if you are truly help us
ሠላም ጤና ይስጥልኝ
ስራ ፈላጊ ለመሆን መጀመሪያ እነዚህን ነገሮች ማንበብ ይገባል ስለዚህ እኔ ብዙጊዜ የአንተን ፁሁፎች አነባቸዋልሁ እና በጣም ጥሩ ጥሩ ነገሮች አሉት ስለዚህ ያለህን እውቀት ለአንተ ብቻ ሳይሆን ለሌላውም እየተጠቀምክበት ስለሆነ ከፍ ያለ ምስጋር አለኝ አመሰግናለሁ ቤቲ ከአዲስ አበባ
ሠላም ጤና ይስጥልኝ
ስራ ፈላጊ ለመሆን መጀመሪያ እነዚህን ነገሮች ማንበብ ይገባል ስለዚህ እኔ ብዙጊዜ የአንተን ፁሁፎች አነባቸዋልሁ እና በጣም ጥሩ ጥሩ ነገሮች አሉት ስለዚህ ያለህን እውቀት ለአንተ ብቻ ሳይሆን ለሌላውም እየተጠቀምክበት ስለሆነ ከፍ ያለ ምስጋር አለኝ አመሰግናለሁ ቤቲ ከአዲስ አበባ
ይህ በጣም ጠቃሚ ምክርህ ሁሌም ይቀጥል
ይህ በጣም ጠቃሚ ምክርህ ሁሌም ይቀጥል
Add new comment