Skip to main content
የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ

የ2023 አባልነት ክፍያዎን በባንክ ወይም በቪፕስ እንዲያስገቡልን በትህትና እንጠይቃለን።
ባንክ፤ 05401729420
ቪፕስ፤ 500424
የዓመታዊ ክፍያ መጠን፤
ለአዋቂ፤ ከ200 ክሮነር አንስቶ
ለህጻናት፤ 80 ክሮነር።
ክፍያውን ሲፈጽሙ "medlemskontingent" የሚለውን መልዕክት ያካቱበት።

በቃለ ምልልስ የሚጠበቁ "ጥያቄና መልሶች"

Ehiopian community in Norway ecn defin oslo norge defin etiopisk forening i norge

በቃለ ምልልስ የሚጠበቁ "ጥያቄና መልሶች"

ብስና አቀራረብን ከማየታችን በፊት አንዳንድ ሊጠየቁ የሚችሉ ጥያቄዎችን በዝርዝር እናያለን፡፡ ብዙ አይነት ጭያቄዎች አሉ፡፡ እንደ ስራው አይነትና ፀባይ ቢለያዩም ተደጋግመው የሚጠየቁ ጥያቄዎች የሚከተሉትን ይመስላሉ፤

1. ስለ መስሪያ ቤታችን ምን ያውቃሉ?
2. እርስዎን ለምን እንቀጥረዎታለን?
3. ምን አይነት አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ ይችላሉ?
4. ከአምስት አመታት በኋላ እራስዎን እንዴት ያዩታል?
5. ጠንካራ ጎንዎ ምንድነው?
6. ደካማ ጎንዎ ምንድነው?
7. አሁን ምን እየሰሩ ነው?
8. ደመወዝዎ ስንት እንዲሆን ይፈልጋሉ?

1. ስለ መስሪያ ቤታችን ምን ያውቃሉ?

ስለ መስሪያ ቤቱ ለማወቅ ለቃለ ምልልስ በተጠሩ ጊዜ አንዳንድ ቁልፍ መረጃዎችን ቢያሰባስቡ በጣም ይጠቅምዎታል፡፡ ከነዚህም መረጃዎች አንዳንዶቹ፤ መስሪያ ቤቱ ከተመሰረተ ስንት ጊዜ እንደሆነው፣ ምን አይነት አገልግሎትና ምርት እንደሚያቀርብ፣ ደንበኞቹ እነማን እንዴሆኑ፣ ስንት ሰራተኞች እንዳሉት ወዘተ ናቸው፡፡ የምንኖርበት ዘመን የመረጃ ዘመን ስለሆነ መስሪያ ቤቱን በመጠኑ ለማወቅ የተለያዩ ምንጮችን መገልገል ይቻላል፡፡ ለምሳሌ መስሪያ ቤቱ የራሱ የኢንተርኔት ገጽ ሊኖረው ስለሚችል ብዙ ነገር እዛ ያገኛሉ፡፡ ካልሆነም ሌሎች የጽሁፍ መረጃዎችን መፈለግ ይቻላል፡፡ ሰውም መጠየቅ ይቻላል፡፡

2. እርስዎን ለምን እንቀጥረዎታለን?

መስሪያ ቤቱ እርስዎን መርጦ እንዲቀጥርዎት ደግሞ ጉረኛ ሳይመስሉ ታታሪ ሰራተኛ መሆንዎን ማስረዳት ተገቢ ነው፡፡ ለምሳሌ ስራው ከትምህርትዎ፣ ከፍላጎትዎና ከልምድዎ ጋር የተያያዘ መሆኑን ሊጠቅሱ ይችላሉ፡፡ ወደፊትም ለማደግና ለመሻሻል ስለሚፈልጉ ስራው ለርስዎ ጥሩ በር ከፋች ሊሆንልዎት እንደሚችልም መጥቀስ ይቻላል፡፡ ስለዚህ ለስራው እርስዎ ተስማሚ እጩ መሆንዎን ማሳመን ይችላሉ፡፡

3. ምን አይነት አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ ይችላሉ?

ከአዲስ ነገር ጋር እራስዎን ፈጠን አርገው ስለሚያለማምዱት ባጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማ መሆን እንደሚችሉ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ተጨባጭ የሆነ ውጤትም ለማስገኘት ታታሪ ሆነው እንድሚሰሩ መጥቃስ ይቻላል፡፡ በመስሪያ ቤቱ ላይ ለውጥ አመጣለሁ እንዳይሉ ግን ይጠንቀቁ፡፡ በኋላ እንደሁኔታው እና እንደ ስራው ድርሻ ይደርሱበታል፡፡ ያኔም ቢሆን በተግባር እንጂ ለውጥ አመጣለሁ እያሉ አይደለም።

4. ከአምስት አመታት በኋላ እራስዎን እንዴት ያዩታል?

ከአምስት አመታት በኋላ ምን እንደሚመስሉ መገመት አስቸጋሪ ነው፡፡ አንዳንድ ወገኛ ስራ ቀጣሪዎች ግን ሊፈታተኑ ይፈልጋሉ። ቢሆንም ግን የተለያዩ አላማዎች ሊኖርዎት ይገባል፡፡ ለምሳሌ ስለቤተሰብ፣ ስለስራ፣ የተለያዩ ነገሮችን ስለማድረግ እና ስለ ስኬታቸው ወዘተ፡፡ ህይዎት እራሷ ትምህርት ቤት እንደመሆኗ መጠን በሚቀጥሉት አመታት ውስጥ በተለያዩ ነገሮች ላይ የበለጠ በእውቀት እንደሚዳብሩ መግለጽ አይከፋም፡፡

5/6. ጠንካራና ደካማ ጎን፤

ብዙዎቻችን ከደካማ ጎን ይልቅ ጠንካራ ጎናችንን መናገር ይቀለናል፡፡ ጠንካራ ጎንዎን ሲናገሩ ጉራ እንዳይመስል ጓዴኞቼ እንዲህና እንዲህ ይሉኛል ማለቱ ይሻላል፡፡ ለምሳሌ በማዳመጥ፣ በፍላጎት፣ የትርፍ ጊዜ እንቅስቃሴዎን፣ አቀራረብዎን፣ የተለያዩ እይታዎን ወዘተ በተመለከተ ሊሆን ይችላል፡፡
ሰው የራሱን ደካማ ጎን ለመናገር ከሆነ ግን ያስቸግራል፡፡ ሆኖም ግን ሰው ፍፁም አይደለምና ደካማ ጎንም ሊኖርዎት ይገባል፡፡ ይህንን ሲናገሩ ግን ድፍን ያለ ደካማ ጎንዎን መናገር የለብዎትም፡፡ ለምሳሌ ወደ ትልቅ ከተማ ስሄድ ፎቆችን መቁጠር ስለለመደብኝ መንገደኞች ጋር መጋጨት ለምዶብኛል ማለት ጭልጥ ያለ ሁለት አይነት ሞኝነት ነው፡፡ በምትኩ ግን “ ጓደኞቼ ግትር አይነት ነህ፤ ምክንያቱም አንድ ጊዜ የተባለውና የታቀደው ነገር ሳያልቅ በቂ እረፍት አታደርግም " ይሉኛል ማለቱ ይሻላል፡፡ ግትር አይነት ቢሆኑም በዕቅድ መመራትዎን ያሳውቅልዎታል፡፡ እራስዎን የሚያረክስ ነገር ቢጠየቁም ስራ ለማግኘት እስከመጡ ድረስ እራስዎን ሙሉ በሙሉ ማርከስ የለብዎትም፡፡ በአርካሹ መልስዎ ይዘት ውስጥ ለስራ ሰጪው ክፍል የሚጥቅም ነገር ማዘል አለበት፡፡ በምሳሌው እንደተረዱኝ ተስፋ አለኝ፡፡

7. አሁን ምን እየሰሩ ነው?

ብዙውን ጊዜ ስራ ቀጣሪወች አሁን ያሉበት ሁኔታ ምን እንደሚመስል ማወቅ ይፈልጋሉ፡፡ ይህንን ከተጠየቁ አሁን የሚያደርጉትንና የሚሰሩትን ባጭሩና በዝርዝር ማስረዳት አለብዎት፡፡ ስራ እሚቀይሩም ከሆን አሁን ያሉበት የስራ ሁኔታ ሊሆን ይችላል፡፡ በጉኑ ደግሞ ስፖርት የሚሰሩ ከሆነ ስፖርት እሰራለሁ ማለቱ አይከፋም፡፡ አካልዎ ሲታይ ግን ስፖርት የማይሰራ ሆኖ ማጋለጥ የለበትም፡፡ ገና ከት/ቤት የወጡ ከሆነም ስለመጨረሻው ትልቁ ፕሮጀክትዎ ዙሪያ ሊሆን ይችላል፡፡ አሁን ስራ ብቻ የሚፈልጉም ከሆነ የከተማ አውደልዳይ እንዳይመስሏቸው በትርፍ ጊዜዎ የተለያዩ ነገሮችን እንደሚያደርጉ መጥቀሱ አይከፋም፡፡ ለምሳሌ በጎ አድራጎት ሊሆን ይችላል፡፡ ዋናው ነገር ግን አሁን እርስዎ ለራስዎና ለአካባቢዎ የሚጠቅምና ፍሬማ ነገር የሚያደርጉ መሆንዎን የቀጣሪወቹ ግምት ውስጥ ለመግባት አለበት፡፡

8. ደመወዝዎ ስንት እንዲሆን ይፈልጋሉ?

ደመወዝስ? ጥያቄው አስቸጋሪ ነው፡፡ ግን ስለመስሪያ ቤቱ አጥንተው ከሆነ የደመወዙን መጠንና አካባቢ ያውቁታል፡፡ ከት/ቤት በቅርቡ የጨረሱ ከሆነ፣ የስራ ልምድ ካለዎት፣ የመስሪያ ቤቱ አይነት፣ የሰራው አይነትና ሃላፊነት የደመወዙን መጠን ይወስነዋል፡፡ ቁጥር ከመጥራትዎ በፊት ግን “ለኔ ለእድገት በር ከፋችና የምወደውን ስራ ማግኘት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ይኸን ስራ ለማግኘት ያመለከትኩት ለዚሁ ነው “ ብለው ቢጀምሩ ነገሮች ይለሳለሳሉ፡፡ ቁጥርም መጥራት ካስፈለገ ምክንያታዊ ሆኖ ጥሩ ደመዎዝ መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡ እርካሽ ደመወዝ መጥራት አያስፈልግም፤ ምክንያቱም የስራ ለማኝ ያስመስላል፡፡

ፋንታው ተሰማ
ለ ኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ፡፡

አስተያየት ይስጡ፤

ይርጋ (not verified) Thu, 06/04/2015 - 09:53

በጣም ያምራል ። አስተማሪ እና ወሳኝ ሙያዊ ማብራሪያ ኑዉ። ይግፋበት። እግዚአብሔር ይስጥልን።

tadesse yibeltal (not verified) Tue, 11/17/2015 - 16:55

I am from Ethiopia. I graduate BA degree in sociology from University of Gondar. I have intense feeling to learn MA in sociology or social work. But financially I can't. If there is opportunity please kindly help me. Thanks. atsedeyeabsira(at)gmail.com

Nuredin Abdi (not verified) Fri, 05/20/2016 - 00:56

Thanks very much for posting this essentials information.

Wendesen Feke (not verified) Sat, 07/09/2016 - 09:56

በጣም ጠቃሚ መረጃ ነው። በተለይ ለአዲስ ተቀጣሪዎች ወሳኝና ቁልፍ መረጃ መሆኑን ተገንዝቢያለሁ። በበኩሌ አመሰግናለሁ።

ጀማለል አህመድ (not verified) Sun, 07/17/2016 - 09:57

የእቅድ ዝግጅት ክትትል ግምገማ ባለሙያ

sra felagi (not verified) Sat, 09/17/2016 - 09:58

konjo mkr new bezihu ketlu

ጌትነት አያሌው (not verified) Wed, 09/28/2016 - 09:59

በጣም ገቢ የሆነ ነገር ስላሥነበባችሁኝ አመሠግናለሁ

Add new comment

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.
x

Please add some content in Animated Sidebar block region. For more information please refer to this tutorial page:

Add content in animated sidebar