Skip to main content
የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ

የ2023 አባልነት ክፍያዎን በባንክ ወይም በቪፕስ እንዲያስገቡልን በትህትና እንጠይቃለን።
ባንክ፤ 05401729420
ቪፕስ፤ 500424
የዓመታዊ ክፍያ መጠን፤
ለአዋቂ፤ ከ200 ክሮነር አንስቶ
ለህጻናት፤ 80 ክሮነር።
ክፍያውን ሲፈጽሙ "medlemskontingent" የሚለውን መልዕክት ያካቱበት።

ቃለ ምልልስ፣ አቀራረብና ልብስ፤

Ehiopian community in Norway ecn defin oslo norge defin etiopisk forening i norge

ቃለ ምልልስ፣ አቀራረብና ልብስ፤

ቃለ ምልልስ ሲጠሩ ምን ልልበስ? ምን ልጫመት? ምን ልኳኳል? እያሉ ማሰብ አይቀርም፡፡ ልብስ የእርቃን መሸፈኛ ብቻ ነው ብሎ ችላ ማለትም አያስፈልግም፡፡ እንደ አገሩና አየሩ ሁኔታ ቢሆንም ገላዎን ታጥበው ንፁህና ለሰውነትዎ የሚስማማ ልብስ ለብሰው ከተጫመቱ በቂ ነው፡፡ ከረባት የግድ ማድረግ የለብዎትም፡፡ ለጋብቻ እንደተጠራ አሸብርቆ ወይም አጊጦ መሄድም አያስፈልግም፡፡ ባርኔጣ ወይም ኮፍያ የሚጠቀሙ ከሆነ ቃለ ምልልሱ ሲካሄ በጭራሽ መደረግ የለበትም፡፡ ለማንኛውም ባርኔጣና ኮፍያ ቤት ውስጥ ማድረግ ቦታው አይደለም፡፡ ቀለሙ ፈዘዝ ያለ ልብስ መምረጥ እይታውን ተፈጥሯዊ ያደርገዋል፡፡ የቀለሙ ቅንብርና ለሰውነት የሚስማማ ልብስ መምረጥና መጠቀም እራሱ ችሎታ ነው፡፡ ለዚህ እኮ ነው ስንቱ በየመንገዱ ተንከራፎ የምናየው፡፡ ተሳሳትኩ?

ለዚህ ለእርስዎ የሚስማማዎትን የልብስና የጫማ አይነት መምረጥ ይኖርብዎታል፡፡ ጥፍር መከርከምና ፀጉር መበጠር አለበት፡፡ ከሩቅ የሚጣራ ሽቶ ያስገምታል፡፡ የከንፈር ቀለምና ኩላኩል ነገርም ማብዛት አያስፈልግም፡፡ ደረትም ባይጋለጥ ጥሩ ነው፡፡ ለምሳሌ ወንዶች አንገት የሚደርስ ሙሉና ክብ ሹራብ ለብሰው ኮት ወይም ጥሩ ጃኬት ቢደርቡበት ያምርባቸዋል፡፡ ሴቶች አመልካቾች ደግሞ ከልብሳቸው ቀለም ጋር የሚስማማ ሻሽ ነገር አንገታቸው ላይ ሸብ አድረገው በደረታቸው ላይ ጠልጠል ቢል የሚያምርባቸው ይመስለኛል፡፡ ያየሩ ንብረት ከፈቀደም ሴቶች ቀሚስ ቢለብሱ ይመረጣል፡፡

ፋንታው ተሰማ
ለ ኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ፡፡

አስተያየት ይስጡ፤

ተፈሪ ገርማ (not verified) Sat, 12/23/2017 - 17:09

እጅግ በጣም ጥሩና ገንቢ የሆነ ሊተገበር የሚገባው ምክርና ተሞክሮም ነው፡፡ ግን በእኛ ሀገር 70% በላይ ማለት ይቻላል ቅጥር የሚፈፀመው በዘመድና በሙሥና ያለቨለዚያም በሌላ በሌላ መልኩ ሲሆን ሠጀመሪያውኑ ከስንት አንድ ካልሆነ በቀር መሥፈርቶች ሢወጡ ሊቀጠር ተፈለገውን ግለሠብ ብቻ ያማከለ ሆነው ነው፡፡ይህን የሚለውጥና የሚያጠፋ ነገር ፈጣሪ ያምጣልን፡፡
አመሠግናለሁ

Add new comment

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.
x

Please add some content in Animated Sidebar block region. For more information please refer to this tutorial page:

Add content in animated sidebar