Skip to main content
የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ

የ2023 አባልነት ክፍያዎን በባንክ ወይም በቪፕስ እንዲያስገቡልን በትህትና እንጠይቃለን።
ባንክ፤ 05401729420
ቪፕስ፤ 500424
የዓመታዊ ክፍያ መጠን፤
ለአዋቂ፤ ከ200 ክሮነር አንስቶ
ለህጻናት፤ 80 ክሮነር።
ክፍያውን ሲፈጽሙ "medlemskontingent" የሚለውን መልዕክት ያካቱበት።

የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይና በዓላት አከባበር፤

Ehiopian community in Norway ecn defin oslo norge defin etiopisk forening i norge

ህበሩ አድስ ዓመት፣ ገና በዓል እና ፋሲካን ከኢትዮጵያውያን ጋር ያከብራል፡፡ ኢድ አልፈጥርና አረፋንም ማህበሩ በአውሮፓውያን 2011 ላይ ማክበር ጀምሯል፡፡ እነዚህ በዓላትን ስናከብር ልክ እንደ ኢትዮጵያ ውስጥ በዕለቱ ቀን ባይሆንም ቀራቢው ቅዳሜ ላይ እናከብራለን፡፡ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በአላትን አብረው ሲያከብሩ ማህበሩን ለማወቅ አንዱ ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡ ቤተሰቦች፣ ግለሰቦችና የሀይማኖት ተቋማት በዕለቱ ላይ እንደሚያከብሩ ይታወቃል፡፡

ለነዚህ በዓላት ዝግጅቶች ማህበሩ ቅድሚያ እንዳለው በሰፊው የታወቀ ነው፡፡ ለብዙ አመታት ሲሰራበትም ቆይቷል፡፡ ከማህበሩ ውጭ በተመሳሳይ ቀን ላይ ዝግጅት የሚያደርጉ አካላት ቀደም ብለው ማህበሩን ቢያሳውቁት መልካም ነው፡፡ ድርብ ዝግጅቶች እንዳይኖሩ ማህበሩ ከሌሎች አካላት ጋር በጋራ መፍትሄ ለማግኘት ይጥራል፡፡ ማህበሩ ቀራቢው ቅዳሜ ላይ ለማክበር የወሰነበት ምክንያት ውጭ ስለምኖርና ከስራም ሆነ ከትምህርት አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ነጻ የሚሆንበት ቀን ቅዳሜ ስለሆነ ነው፡፡

እነዚህ በዓላት በሰፊውና ባዝናኝ መልኩ እንዲከበሩ ማህበሩ የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል፡፡ ቀን ላይ የልጆችና የቤተሰቦች ዝግጅቶች አሉ፡፡ አንዳንዶቹ እንቅስቃሴዎችም የልጆች ጨዋታ፣ ውድድር፣ ሽልማት፣ የልጆች ዘፈን፣ ምግብና መጠጦች፣ የቡና ስናስርዕት የመሳሰሉት ይዘጋጃሉ፡፡ ምሽት ላይ ደግሞ ከምግብና ከመጠጥ ጋር የሙዚቃ ምሽት አለ፡፡

Add new comment

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.
x

Please add some content in Animated Sidebar block region. For more information please refer to this tutorial page:

Add content in animated sidebar