Skip to main content
የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ

የ2023 አባልነት ክፍያዎን በባንክ ወይም በቪፕስ እንዲያስገቡልን በትህትና እንጠይቃለን።
ባንክ፤ 05401729420
ቪፕስ፤ 500424
የዓመታዊ ክፍያ መጠን፤
ለአዋቂ፤ ከ200 ክሮነር አንስቶ
ለህጻናት፤ 80 ክሮነር።
ክፍያውን ሲፈጽሙ "medlemskontingent" የሚለውን መልዕክት ያካቱበት።

የስራ ማመልከቻ አጻጻፍ፣ ሂደቱና ክትትሉ፤

የስራ ማመልከቻ አጻጻፍ፣ ሂደቱና ክትትሉ፤

Ehiopian community in Norway ecn defin oslo norge defin etiopisk forening i norge

ራ ማመልከቻ የአመልካቹን ማንነት የሚገልጽ ነው፡፡ ስለዚህ ማመልካቻው ሲጻፍ ተገቢ ጥንቃቄና ትኩረት ያስፈልገዋል፡፡ ኮተትም ሳይበዛበት አጠር ብሎ ግልፅና ለመረዳት ቀላል መሆን አለበት፡፡ ቀጣሪዎች ብዙ ማመልከቻዎች ስለሚደርሷቸው እጥር ምጥን ያሉ ማመልከቻዎችን ሊመርጡ ይችላሉ፡፡ እንግዲህ ማመልከቻ ሲፅፉ ቀን፣ የእርስዎ ሙሉ ስምና አድራሻ ይቀድማል፡፡ ከዚያም የስራው አይነት ከነ አርእስቱ ጎላ ብሎ በአርእስት መልክ ገባ ብሎ ይሰፍራል፡፡ ወደ ዝርዝር ከመግባትዎ በፊት ስራውን በተመለከተ መቼና ከማን ጋር በስልክ ጥሩ ውይይት እንደነበረዎት ቢጠቅሱ ይታዎሳሉ፡፡ ከዚያም ይኸን ስራ ለምንና እንዴት እንደፈለጉት ባጭሩና በዝርዝር ያቀርባሉ፡፡ የትምህርት ጊዜ፣ የስራ ልምድ፣ በትርፍ ጊዜ የሚደረጉ የተለያዩ ዝንባሌዎች፣ ወዘተ እራሱን በቻለ ገጽ ላይ እጥር ምጥን አድርጎ ማቅረብ የተለመደ ነው፡፡

በተጨማሪም አመልካቹ ባሁኑ ጊዜ ምን እንደሚያደርግና ህይወቱም ምን እንደሚመስል በገንቢ መልክና ባጭሩ ቢያቀርብ ማመልከቻውን ሁለገብ ያደርገዋል፡፡ አመልካቹ በራሱ አስፈላጊና ጠቃሚ ናቸው ብሎ ያመነባቸውን የራሱን ሁኔታዎችና ልዮ ችሎታዎች ቢጠቅስ ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም፡፡ በመጨረሻም እርስዎን የሚያዉቁዎትንና የጠየቋቸውን የሁለት ወይም ሶስት ተጠሪ ግለሰቦች ስም ከነሙያቸው ያሰፍራሉ፡፡ የተጠሪዎቹን ስም ለቃለ ምልልስ ሲቀርቡም ማሳወቅ ይችላሉ፡፡ ይኸን እንደ ምርጫዎና እንደ ስራው ማስታወቂያ አይነትና ፍላጎት ይለያያል፡፡ ተጠሪዎቹም ድንገት ተደውሎላቸው እንዳይደናገሩ ጉዳዩን በቅድሚያ ይንገሯቸው፤ ያስታውሷቸውም፡፡

ማመልከቻውም ከተላከ ከሶስት እስከ አምስት ቀናት በኋላ ከዚህ በፊት ያነጋገሩት ሰው ደግሞ መደወል ጥሩ ነው፡፡ ስልኩንም እራሱ ሰውዬው ካነሳው/ችው በስም “ ሰላም እከሌ” ብሎ ንግግር መጀመር ነው፡፡ ለምሳሌ “በዚህ ቀን ላይ ስለዚህ ስራ ተነጋግረን ነበር፡፡ ማመልከቻ ልኬአለሁ፡፡ ስለ ማመልከቻው ምን ይመስልዎታል? ሌላ ተጨማሪ ነገር የምትፈልጉት ካለ እልካለሁ፡፡” ብሎ መጠየቅ ይጠቅማል፡፡ ማመልከቻው እስከዛሬ ድረስ ያልተነበበ ከሆነ አርስዎ ስለደወሉ ማመልከቻው ከተቀመጠበት ተነስቶ ወይም ተመዞ አሁን ሊነበብ ይችላል።

ዋናው ቁም ነገር ግን አርስዎ አሁን እራስዎን እንደገና ለሁለተኛ ጊዜ አስተዋወቁ፡፡ የራስዎንም ማመልከቻ በደንብ እየተከታተሉ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ያነጋገሩትን ሰው በስም አስታወሱ፡፡ ይህንንም ስራ ለማግኘት ፍላጎትዎን እንደገና አሳዩ፡፡ ማመልካቻውም ከንብብሩ ላይ ተነስቶ ወይም ተመዞ ታየለዎት፡፡ ቀጣሪውም አርስዎን በቀላሉ ያስታውሰዎታል፡፡

ንግግሩም በሚካሄድበት ጊዜ እርስዎ እንደ ስራ ለማኝ ወይም ተስፋ ቢስ አይነት ሆነው መቅረብ የለብዎትም፡፡ ባነጋገር ሁኔታና በድምፅ ቃና በራስዎ የሚተማመኑ መሆንዎን ማሳወቅ መቻል አለብዎት፡፡ ይህ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ላልተጠበቁ ጥያቄዎችና መልሶች በስልክም ቢሆን ቅሉ ዝግጁ መሆንና በተቻለ መጠን ምክንያታዊ ጥያቄ ማቅረብና መልስም መስጠት ከቀጣሪው ነጥብ ያሰጣል፡፡ መጨረሻ ላይም አመስግኖ ለቃለ ምልልስ እንድምጠራ ተስፋ አደርጋለሁ ሳይሆን ለቃለ ምልልስ እንደምጠራ እጠብቃለሁ ብለው በጨዋነት የስልኩን ንግግር መደምደም ነው፡፡ ዘንድሮ እኮ በጣም ደፋርና አይን አውጣ ሆንኩኝ ብለው አይስጉ። እንደ ሞኝ ሆነው ካልቀረቡ በስተቀር እስካሁን ድረስ ማመልከቻዎን በትክክል እየተከታተሉ ነው፡፡

ዋናው ነገር ወሬ ሳያበዙ ባጭሩ መጠየቅ፣ መልስ መስጠትና በጊዜው ውይይትዎን መጨረስ ነው።

በሚቀጥሉት ቀናት ወይም ሳምንታት ውስጥ ለቃለ ምልልስ ካልተጠሩ ከላይ በተጠቀሰው መልኩ ሌላ ስራ ለማግኘት አደናውን መቀጠል ነው፡፡ ለቃለ ምልልስ ከተጠሩ ደግሞ እሰየው ነው፡፡ አንድ እርምጃ ወደፊት፡፡ አሁን ደግሞ ይህንን ስራ ለማግኘት ምን መደረግ እንዳለበት አብረን እናያለን፡፡

ለማስታወስ ያህል የመጀመሪያው የስራ አፈላለግ ስልት ላይ በዝርዝር የሚከተሉትን ነጥቦች አይተናል፤

ለስራ ፍለጋ ቅድሚያ ዝግጅት፣
ክፍት የስራ ቦታዎች ምን ላይና እንዴት እንደሚዎጡ፣
ማመልካቻ ከመጻፉ በፊት ስለሚደርጉ ቅድመ ዝግጂቶችና፣
የማመልከቻ አጻጻፍና ክትትሉን አይተናል፡፡
ፋንታው ተሰማ
ለ ኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ፡፡

አስተያየት ይስጡ፤

Anonymous (not verified) Mon, 08/26/2013 - 07:12

ስራ ፈላጊ ለመሆን መጀመሪያ እነዚህን ነገሮች ማንበብ ይገባል ስለዚህ እኔ ብዙጊዜ የአንተን ፁሁፎች አነባቸዋልሁ እና በጣም ጥሩ ጥሩ ነገሮች አሉት ስለዚህ ያለህን እውቀት ለአንተ ብቻ ሳይሆን ለሌላውም እየተጠቀምክበት ስለሆነ ከፍ ያለ ምስጋር አለኝ አመሰግናለሁ ቤቲ ከአዲስ አበባ

ቤቲ (not verified) Sat, 11/16/2013 - 07:17

ስራ ፈላጊ ለመሆን መጀመሪያ እነዚህን ነገሮች ማንበብ ይገባል ስለዚህ እኔ ብዙጊዜ የአንተን ፁሁፎች አነባቸዋልሁ እና በጣም ጥሩ ጥሩ ነገሮች አሉት ስለዚህ ያለህን እውቀት ለአንተ ብቻ ሳይሆን ለሌላውም እየተጠቀምክበት ስለሆነ ከፍ ያለ ምስጋር አለኝ አመሰግናለሁ ቤቲ ከአዲስ አበባ

Add new comment

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.
x

Please add some content in Animated Sidebar block region. For more information please refer to this tutorial page:

Add content in animated sidebar