Skip to main content
የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ

የ2023 አባልነት ክፍያዎን በባንክ ወይም በቪፕስ እንዲያስገቡልን በትህትና እንጠይቃለን።
ባንክ፤ 05401729420
ቪፕስ፤ 500424
የዓመታዊ ክፍያ መጠን፤
ለአዋቂ፤ ከ200 ክሮነር አንስቶ
ለህጻናት፤ 80 ክሮነር።
ክፍያውን ሲፈጽሙ "medlemskontingent" የሚለውን መልዕክት ያካቱበት።

አቀራረብ ፊት ለፊት፤

Ehiopian community in Norway ecn defin oslo norge defin etiopisk forening i norge

አቀራረብ ፊት ለፊት፤

ተለያዩ አቀራረቦች ቢኖሩም ማንም ቢሆን ግን የሚመርጠው ቀና የሆነ አቀራረብ ነው። ታዝበው ከሆነ መጥፎ ነገር ቀርቶ ደህና ነገር ላይ እንኳን ሲያስቡ፣ ሲናገሩና ሲመለከቱ ሳያውቁት በተለምዶ ፊታቸው የሚኮሳተር ሰዎች ጥቂት አይደሉም። በጊዜው ለኛ ባይታየንም ተመልካች ያውቀዋል፡፡

የመጀመሪያ ግምገማ ወሳኝ እስከሆነ ድረስ ስራ ፍለጋ ሄደው ፊትዎን አኮሳትረው እራስዎን እንዳይቀጡ፡፡ አደራ፡፡ ሲናገሩና ሲያስቡ ፊትዎ ምን እንደሚመስል በመስታወት ወይም በጓዴኛዎ ቀድመው መለማመድ ይችላሉ፡፡

ለቃለ ምልልስ የሚሄዱበትን ቦታ ቀደም ብለው አድራሻውን ካዎቁ ከሃሳብና ጭንቀት ይድናሉ፡፡ በቀጠሮውም ሳይዘገዩ አምስት ደቂቃ አካባቢ ሲቀረው በስፍራው መገኘት የተሻለ ምርጫ ነው፡፡ እጅዎንም ካላበዎት በመሃረም ነገር ያድርቁት፡፡ በነገር የሚያፋጥጠዎት ቀጣሪ ክፍል በሚቀበልዎት ጊዜ አንገትዎን ቀና፣ ፊትዎንና ትካሻዎን ዘና አድርገው ፊት ለፊት እያዩ ጠበቅና ሞቅ ያለ ሰላምታ ይስጡ፡፡ ከዚህ በፊት በስልክ ያነጋገሩት ግለሰብ መጥቶ ከተቀበለዎትና በስሙ እርግጠኛ ከሆኑ፤ “ከርስዎ ጋር ከዚህ በፊት ስለስራው ተነጋግረናል” ብለው መጥቀስ ይችላሉ፡፡

ወደ ውይይት ክፍሉ ሲወሰዱ መተላለፊያው፣ ጓዳውና ኮተቱ የበዛበት ከሆነ፤ በኋላ ሲወጡ መውጫው እንዳይጠፋዎት ያስታውሱ፡፡ በኋላ እንዳይታዘቡዎት፡፡ እኔ ኣንድ ጊዜ ተሸውጃለሁ። በኋላ ላይ እራሴን በመዳፌ እየመታሁ አንተ ደንቆሮ ብያለሁ፡፡ ግን ምንም ጥቅም የለውም፡፡ ትምህርት መውሰድ ብቻ፡፡

ክፍሉም ውስጥ እንደገቡ ሌሎች ሁለት አካባቢ የሚሆኑ በነገር የሚያፋጥጡ ግለሰቦች መኖራቸው ስለማይቀር ለነሱም ሞቅ ያለ ሰላምታ ያቅርቡ፡፡ ስማቸውንም ለማስተዎስ ይሞክሩ፡፡ ክፍሉም ጥሩ ከሆነ ወይም ጠረንጴዛው በደንብ የተሰናዳ ከሆነ ወይም ግድግዳው ላይ ጥሩ ስዕል ካዩ ጥሩ መሆኑን ካደነቁ ጥሩ ታዛቢ መሆንዎን ያሳያል፡፡ ካላማረዎት ግን ማስመሰል ስለሆነ አፍዎን አያበላሹ፡፡ ሲቀመጡ ሌሎቹን መጀመሪያ ማስቀደም ተገቢ ነው፡፡
ከተቀመጡ በኋላ ተዝናንተው በስርአት ይቀመጡ እንጂ ዝልፍልፍ አይበሉ፡፡ የፈሩም አይምሰሉ፡፡ እግርዎን ሳያነባብሩ ቁጭ ብለው እጆችዎ ጭነዎ ላይ አርፈው አገጭዎ ፎቶ እነደሚነሳ ሰው ቀና ብሎ፤ ትካሻዎና ወገብዎ ሲዝናና ከተሰማዎት ግሩም አቀማመጥ ይመስለኛል፡፡ ፊትዎ ዘና ማለቱን ሁልጊዜ ያስታውሱ። ይህ አቀማመጥ እንደተጠበቀ ሆኖ እጅዎንም ሆነ ሰውነትዎን በተገቢው ለማንቀሳቀስ ምቹ ነው፡፡ በሚናገሩ ጊዜ የጠየቀዎትን ግለሰብ በቀጥታ እያዩ ቢሆንም ሌሎቹንም ለአፍታ ገረፍ ማድረግ አለብዎት፡፡ ቀጣሪዎቹ በሚናገሩ ጊዜ እንዳያቋርጧቸው ጠንቀቅ ይበሉ፡፡ አቀርቅረው አያውሩ፡፡ የሚናገሩት ቋንቋም አንድ ሆኖ ግልፅና ሙሉ መሆን አለበት፡፡ አፉን እንደሚፈታ ህጻን ልጅም መንተባተብ አይገባም፡፡ ቀጣሪዎቹ “ምን አሉ?” እንዲሉዎት እድል አይስጡ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ካልሆነ በስተቀር እጅዎን አያወናጭፉ፡፡ ነገርን ባጭሩ ይመልሱ እንጂ ያለአስፈላጊ ብዙ ትንተና ውስጥ ገብተው ነገር አይበላሽብዎት፡፡ የማያውቁት ነገር ከተጠየቁ “ይህንን አላውቅም” ማለት ይሻላል፡፡ ሲያዳምጡም ሆነ ሲናገሩ የፊትዎ ገጽታ የዘናና የተዝናና መሆኑን በውስጥዎ ያስታውሱ፡፡ አቀራረብ!!

ቃለ ምልልሱም እንዳለቀ ተሰናብተውና አመስግነው ካመሰገኑ በኋላ ውልቅ ብሎ መውጣት ነው፡፡ ውጤቱን በቀናት ወይም በሳምንታት ጊዜ ውስጥ መስጠት የተለመደ ነው፡፡ ይቅናዎት!!

እዚህ ድረስ ስላነበቡ አመስግናለሁ!
ፋንታው ተሰማ
ለ ኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ፡፡

አስተያየት ይስጡ፤

teklu mekonen (not verified) Sat, 11/14/2015 - 03:59

First of all,i will say thank u for the ethionorway.org. next of that i have a need to get job.thank u.

Add new comment

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.
x

Please add some content in Animated Sidebar block region. For more information please refer to this tutorial page:

Add content in animated sidebar