የ2023 አባልነት ክፍያዎን በባንክ ወይም በቪፕስ እንዲያስገቡልን በትህትና እንጠይቃለን።
ባንክ፤ 05401729420
ቪፕስ፤ 500424
የዓመታዊ ክፍያ መጠን፤
ለአዋቂ፤ ከ200 ክሮነር አንስቶ
ለህጻናት፤ 80 ክሮነር።
ክፍያውን ሲፈጽሙ "medlemskontingent" የሚለውን መልዕክት ያካቱበት።
ስራ ፍለጋና ቃለ ምልልስ፤

ስራ ፍለጋና ቃለ ምልልስ፤
አሁን ደግሞ ለቃለ ምልልስ ከተጠሩ ምን አይነት ዝግጅትና ትኩረት ማድረግ አንዳለብዎት አብረን እናያለን። ለቃለ ምልልስ መጠራት ማለት ስራውን ለማግኘት እጩ መሆን ማለት ነው፡፡ ሆኖም ግን አሁንም ሌሎች ተፎካካሪ አመልካቾች እንደርስዎ ለቃለ ምልልስ ስለሚጠሩ ውድድሩ ተፋፋመ እንጂ አላለቀለም፡፡ የሚዎዱትንና የፈለጉትን ስራ ማግኘት ያስደስታል፡፡ ያረካልም፡፡ የፈጠራ ችሎታዎንም ከተጠቀሙበት እድገትዎ ይጨምራል። ደመወዝም የቤተሰብ ማስተዳደሪያና የተለያዩ ወጭወችን መሸፈኛ ስለሆነ ለማንም ቢሆን ስራ አስፈላጊ ነው፡፡ ይኸን ስራ ለማግኘት እራስዎን አስማምተውና አቀራረብዎን አሳምረው ለቀጣሪው አካል መሸጥ አለብዎት፡፡ ቀጣሪውም አካል እስካሁን ድረስ በድምጽና በማመልከቻ ብቻ ያውቅዎታል፡፡ አሁን ግን በአካል ተገኝተው ፊት ለፊት እንዲዎያዩ ተጋብዘዋል፡፡ ስለዚህ ልዩ የሆነ ዝግጅት ማድረግም አለብዎት፡፡ ለዕድል ቦታ መስጠት የለብዎትም፡፡
መቼም ለቃለ ምልልስ ሲጠሩ፤ እንዳው ቀጣሪዎች ሲያዩኝ ይወዱኝ ይሆን? ምን ይጠይቁኝ ይሆን? ምን አይነት መልስ እሰጥ ይሆን? ምን ልልበስ? ወዘተ እያሉ ግራ መጋባት አይቀርም፡፡ እንዴት እንደሚዘጋጁ የማውቀውን በደንብ እነግረዎታለሁ፡፡ ምን አይነት መልስ እንደሚመልሱ ግን ምን አይነት ጥያቄዎች እንደሚጠየቁ ስለማላውቅ ሊጠየቁ የሚችሉትን ጥያቄዎች ብቻ አብረን እናያለን፡፡ መልሶቹ ምናልባት ለርስዎ ሁኔታና ገጠመኝ ፊት ባያደርጉም መንደርደሪያ መልሶች ይሆኑዎታል፡፡ በጣም ብዙ ነገሮች ግምትና ቁጥር ውስጥ ይገባሉ፡፡ ለምሳሌ አቀራረብዎ አንሶ ትምህርትና የስራ ልምድ ብቻቸውን ግቡን አይመቱም፡፡ አቀራረብ ለስራ ማግኘትም ሆነ ለማህበራዊ ኑሯችን ጭምር እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ አቀራረብ ወሳኝ ከመሆኑ የተነሳም ስራ ለማግኘት ከመቶ ግማሹን ያህል ሊቆጠር ይችላል፡፡ ልብ ይበሉ!
ፋንታው ተሰማ
ለ ኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ፡፡
አስተያየት ይስጡ፤
Electrical Engineer
በጣም ጥሩ አስተማሪ ነው። አመሰግናለሁ
Add new comment