Skip to main content
የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ

የ2023 አባልነት ክፍያዎን በባንክ ወይም በቪፕስ እንዲያስገቡልን በትህትና እንጠይቃለን።
ባንክ፤ 05401729420
ቪፕስ፤ 500424
የዓመታዊ ክፍያ መጠን፤
ለአዋቂ፤ ከ200 ክሮነር አንስቶ
ለህጻናት፤ 80 ክሮነር።
ክፍያውን ሲፈጽሙ "medlemskontingent" የሚለውን መልዕክት ያካቱበት።

የኢማኖ ፕሮጀክቶች 2008 ላይ፤

Ehiopian community in Norway ecn defin oslo norge defin etiopisk forening i norge

ሚከተሉት ፕሮጀክቶች የተነደፉት በአውሮፓውያን 2008 ውስጥ እንዲጠናቀቁ ነው፡፡ ፕሮጀክቶቹ እንዴት እንደሚጠናቀቁ ኮሚቴው እቅድና የስራ ድርሻ ካከፋፈለ በኋላ ለተግባራዊ እንቅስቃሴ ማስታወቂያ ያወጣል፡፡ ኢትዮጵያውያንም ተካፋይ እንደሚሆኑ ማህበሩ በኢትዮጵያውያን ላይ ይተማመናል፡፡

የኢትዮጵያ ቀን 2008
ኢማኖ ኖርዌይ ውስጥ እንደ ድርጅት ከተመዘገበ 10 ዓመት ስለሚሞላው ቀኑ ይከበራል፡፡ ስለ ማህበሩ ታሪክ ባጭሩ፣ እንቅስቃሴወችና ገለጻ ይደረጋል፡፡ ይኸን ተከትሎ ፕሮጀክቶችም ይካሄዳሉ፡፡ አውደ ትዕይንት፣ ፈሊጥ፣ የተለያዩ ምግቦች ወዘተ ይኖራል፡፡ ቦታው ኦስሎ ሶፊየንበርግ ፓርክ ነው፡፡ ቅዳሜ ነሃሴ 16 ከ1200 - 2000. ዝግጅቱ ለሁሉም ክፍት ነው፡፡

የኢትዮጵያውያን የበጋ ስፖርት ፊስቲቫል፤
ፌስቲቫሉ የእግር ኳስ፣ የመረብ ኳስ፣ የጠረጴዛ ኳስና የሩጫ ውድድር ይገኝበታል፡፡ ልክ እንደ 2007 ሴትና ወንድ ከልጆች እስከ አዋቂዎች ብዙ ኢትዮጵያውያን የሚሳተፉበት ፌስቲቫል ነው፡፡ በማህበሩና በህብረተሰቡ ተወዳጅና የሚጠበቅ ፌስቲቫል ነው፡፡

የትምህርት እርዳታ፤
ለታዳጊ ወጣቶችና ወጣቶች በሳምንት ከ1-2 ጊዜ የትምህርት እርዳታ መስጠት፡፡

የባህልና ያብሮ መዋሀድ ጉባኤ፤
ቤተሰብና አብሮ መኖርን በተመለከተ እውቀትን ማስፋትና ማሳደግ፡፡

የባህልና ባህሪ ለውጥ፤
ኖርዌይ ውስጥ ለመኖር ቀለል እንዲል አስተሳሰብና ባህሪን በተመለከተ ጉባኤ ማድረግ፡፡

ስነ ጥበብና ውህደት፤
ኢትዮጵያውያን ስነ ጥበበኞች በኖርዌጅኛ እንዲጽፉ ማበረታታት፡፡

ከላይ የተጠቀሱት ስድስቱም ፕሮጀክቶች በአውሮፓውያን 2008 ላይ ተጠናቀው ለኦስሎ ኮሙና ሪፖርት ቀርቧል፡፡

Add new comment

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.
x

Please add some content in Animated Sidebar block region. For more information please refer to this tutorial page:

Add content in animated sidebar