የ2023 አባልነት ክፍያዎን በባንክ ወይም በቪፕስ እንዲያስገቡልን በትህትና እንጠይቃለን።
ባንክ፤ 05401729420
ቪፕስ፤ 500424
የዓመታዊ ክፍያ መጠን፤
ለአዋቂ፤ ከ200 ክሮነር አንስቶ
ለህጻናት፤ 80 ክሮነር።
ክፍያውን ሲፈጽሙ "medlemskontingent" የሚለውን መልዕክት ያካቱበት።
የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ ይጠቅማል!
ecn
16 November 2007

የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ አንደኛውና ዋናው እቅዱ ኖርዌይ ውስጥ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መካከል ስምምነትና ውህደትን የበለጠ ለማዳበር ነው፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ ትምህርታዊ እንቅስቃሴወችና ውይይቶች ይደረጋሉ፡፡ እርስዎም የማህበሩ ባለቤትነት እንዲሰማዎት ማህበሩ የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል፡፡
ማህበሩ እንዴት ይጠቅማል?
- ማህበሩ የሚሰጥዎት ዋናው ጥቅም፤ እርስዎ አባል ከሆኑ የመምረጥም ሆነ የመመረጥ መብት አለዎት፡፡ ሌሎችም ጠቅላላ ጉባኤ በሚሹ ጉዳዬች ላይ የርስዎ ውሰኔ ተጽዕኖ አለው፡፡
- ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ባህል በኖርዌይ ውስጥ ከርስዎ ጋር እውቅናውን ያስፋፋል፡፡ ተጽዕኖ ያደርጋል፡፡ ተሰሚነትም ይኖረዋል፡፡
- ከወገኖችዎ ጋር ባንድ ላይ ሲተባበሩ የማህበሩ ባለቤትነት ይሰማዎታል፡፡ ማህበሩም ከርስዎ ጋር በይበልጥ የታወቀ ይሆናል፡፡
- ማህበሩ ለርስዎና ለሌሎችም እርስበርስ የመማሪያና መረዳጃ መድረክ ይሆናል፡፡
- አባል ከሆኑና ቢያንስ የስድስት ወራት ክፍያ በተከታታይ ወይም ባንድ ጊዜ ከከፈሉ ማህበሩ በሚያዘጋጃቸው ዝግጅቶች ላይ የመግቢያ ዋጋ በ20% ይቀንስልዎታል፡፡
- ማህበሩ በአመት ከ 4 - 6 ጊዚያት ድረስ ዝግጅት ያደርጋል፡፡
- ፕሮጀክቶች በሚፈቀዱ ጊዜ ለታዳጊ ህጻናትንና ወጣቶች አመቱን ሙሉ በሳምንት አንድ ጊዜ የትምህርት እርዳታ ይለግሳል፡፡
- የማህበሩ መረበ ገጽ ላይ ህጻናት በነጻ ፊዴል ይማራሉ፡፡
- ማህበሩ የበሰሉ እና አዋቂ ግለሰቦች ጋር የትብብር ግንኙነት አለው፡፡ እርዳታና ምክር ለሚሹ ኢትዮጵያውያን ማህበሩ እነዚህ አዋቂ ግለሰቦች የሀሳብ እርዳታቸውንና ምክራቸውን እንዲለግሱ ያስተባብራል፡፡
ማህበሩ እንዲጠነክር የርስዎ ተሳትፎና እንቅስቃሴ፤
አባል በመሆን በሀሳብና በገንዘብ ማህበሩን መደገፍ፤ ማህበሩ በሚያዘጋጃቸው በዓላት ላይ መገኘት፤ ማህበሩ በሚያዘጋጃቸው ትምህርታዊ ውይይቶች ላይ መሳተፍ ፡፡
ከላይ የተጠቀሱት ዝርዝሮች ላይ እንደሚያዩት፤ ማህበሩ ያለጥርጥር ይጠቅማል፡፡
Add new comment