ይዘት ➞ መነሻ ➞ አላማ ➞ ማህበሩ እና በአላት ➞ መተዳደሪያ ደንብ ➞ አባል ይሁኑ ➞ መሰባሰቢያ ክለብ ➞ ስፖርትና ባህል 2024
✍ አድራሻ ethionor1@gmail.com
+47 970 02 935
Orgnr. 984047355
☝ አመታዊ ክፍያ ባንክ፤ 05401729420
ቪፕስ፤ 500424
ለአዋቂ፤ ከ200 ጀምሮ
ለህጻናት፤ 80 ክሮነር
ክፍያውን ሲፈጽሙ "medlemskontingent" የሚለውን መልዕክት ያካቱበት።
በቅድሚያ እናመሰግናለን!

የማህበሩ አላማ

ecn defin ethiopia norway amharic ethiopian community

ኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ ዋናው አላማ ኖርዌይ ውስጥ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አገልግሎት ለመጠት ነው። የተለያዩ ትምህርታዊ እንቅስቃሴወችና ውይይቶች ይደረጋሉ፡፡ ለምሳሌ የኖርዌይን ባህልና ወግ ለመልመድ መረጃ ይሰጣል። የኢትዮጵያ ባህልና ወግን ለምስተዋወቅ እንቅስቃሴዎች ይደረጋሉ። እርስዎም የማህበሩ ባለቤትነት እንዲሰማዎት ማህበሩ የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል፡፡
የማህበሩን ሙሉ አላማ አንቀጽ 5 ላይ ማንበብ ይችላሉ!
የመህበሩ ደንብ እና ህግ

ማህበሩ እንዴት ይጠቅማል?

አባል ከሆኑ የመምረጥም እና የመመረጥ መብት አለዎት፡፡ ሌሎችም ጠቅላላ ጉባኤ በሚሹ ጉዳዬች ላይ የርስዎ ውሰኔ ተጽዕኖ አለው፡፡

ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ባህል በኖርዌይ ውስጥ ከርስዎ ጋር እውቅናውን ያስፋፋል፡፡ ተጽዕኖ ያደርጋል፡፡ ተሰሚነትም ይኖረዋል፡፡

ከወገኖችዎ ጋር በአንድ ላይ ሲተባበሩ የማህበሩ ባለቤትነት ይሰማዎታል፡፡ ማህበሩም ከርስዎ ጋር በይበልጥ የታወቀ ይሆናል፡፡

ማህበሩ ለርስዎ እና ለሌሎች እርስበርስ የመማሪያና መረዳጃ መድረክ ይሆናል፡፡

አባል ከሆኑ እና ቢያንስ የስድስት ወራት ክፍያ በተከታታይ ወይም ባንድ ጊዜ ከከፈሉ ማህበሩ በሚያዘጋጃቸው ዝግጅቶች ላይ የመግቢያ ዋጋ በ20% ይቀንስልዎታል፡፡

ማህበሩ በአመት ከ 4 - 6 ጊዚያት ድረስ ዝግጅት ያደርጋል፡፡

ፕሮጀክቶች በሚፈቀዱ ጊዜ ለታዳጊ ህጻናትንና ወጣቶች አመቱን ሙሉ በሳምንት አንድ ጊዜ የትምህርት እርዳታ ይለግሳል፡፡

የማህበሩ መረበ ገጽ ላይ ህጻናት በነጻ ፊዴል ይማራሉ፡፡

ማህበሩ አዋቂ ግለሰቦች ጋር የትብብር ግንኙነት አለው፡፡ እርዳታና ምክር ለሚሹ ኢትዮጵያውያን ማህበሩ እነዚህ አዋቂ ግለሰቦች የሀሳብ እርዳታቸውን እና ምክራቸውን እንዲለግሱ ያስተባብራል፡፡

ማህበሩን ለማጠንከር የርስዎ ተሳትፎና እንቅስቃሴ፤

አባል በመሆን በሀሳብና በገንዘብ ማህበሩን መደገፍ፤ ማህበሩ በሚያዘጋጃቸው በዓላት ላይ መገኘት፤ ማህበሩ በሚያዘጋጃቸው ትምህርታዊ ውይይቶች ላይ መሳተፍ ፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች ላይ እንደሚያዩት፤ ማህበሩ ይጠቅማል፡፡ የርስዎ ተሳትፎ ግን ወሳኝ ነው።

ከታች አስተያየት ወይም ነጥብ ይስጡ!

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
1000
Powered by Commentics

የተሰጡ አስተያየቶች

አስተያየት ገና አልተሰጠበትም። የመጀመሪያው ይሁኑ!