ፕሮጀክት ➞ የ2007 ፕሮጀችት ➞ የ2008 ፕሮጀችት
✍ አድራሻ ethionor1@gmail.com
+47 970 02 935
Orgnr. 984047355

የማህበሩ ፕሮጀክቶች 2007

ecn defin ethiopia norway amharic ethiopian community

ሚከተሉት ፕሮጀክቶች የተነደፉት በአውሮፓውያን 2007 ውስጥ እንዲጠናቀቁ ነው፡፡ ፕሮጀክቶቹ እንዴት እንደሚጠናቀቁ ኮሚቴው እቅድና የስራ ድርሻ ካከፋፈለ በኋላ ለተግባራዊ እንቅስቃሴ ማስታወቂያ ያወጣል፡፡ ኢትዮጵያውያንም ተካፋይ እንደሚሆኑ ማህበሩ በኢትዮጵያውያን ላይ ይተማመናል፡፡

የትምህርት እርዳታ፤ ለታዳጊ ወጣቶችና ለወጣቶች በሳምንት ከ1-2 ጊዜ የትምህርት እርዳታ መስጠት፡፡

ስፖርት፤ መጪው በጋ ላይ የግር፣ የመረብና የጠረንጴዛ ኳስ እና የሩጫ ውድድር ኦስሎ ውስጥ ለኢትዮጵያውያን ይደረጋል፡፡

የባህልና የውህደት ጉባዔ፤ ባህልንና ኖርዌይ ውስጥ መዋሀድን በተመለከተ ጉባዔዎች ይካሄዳሉ፡፡

ጉባዔ ስለ ሲቶች ግረዛ፤ ግረዛ የሚያስከትለውን አጸፋ በተመለከተ ጉባዔዎች ይደረጋሉ፡፡

ደንብና ህግ ኖርዌይ ውስጥ፤ የኖርዌይ ደንብና ህግን ለአዲስ ኢትዮጵያውያንና ሌሎች የበለጠ እንዲያውቁ ማድረግ፡፡

የሴቶች አቅምን ግንባታ፤ የኖርዌይ ህግ ስለ ልጅ፣ ቤተሰብና ትዳር እንዲሁም ዘመናዊ ልጅ አስተዳደግ፡፡

የዕውቀት ፕሮጀክት 2007፤ ክለባችን ውስጥ ቢያንስ ሦስት ኮምፕዩተሮች ይኖሩናል፡፡ የአስሊ መሰረታዊ ትምህርት መስጫ፣ የስራ ፍለጋ ማስተማሪያ፣ የትርጉም ስራዎች መስሪያ፣ ለወጣቶች የቤት ስራ መርጃ ወዘተ ይውላሉ፡፡ ማተሚያ፣ ፋክስ ማድረጊያና ማሰሻ ይኖረናል፡፡

ከታች አስተያየት ወይም ነጥብ ይስጡ!

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
1000
Powered by Commentics

የተሰጡ አስተያየቶች

አስተያየት ገና አልተሰጠበትም። የመጀመሪያው ይሁኑ!