የሚከተሉት ፕሮጀክቶች የተነደፉት በአውሮፓውያን 2008 ውስጥ እንዲጠናቀቁ ነው፡፡ ፕሮጀክቶቹ እንዴት እንደሚጠናቀቁ ኮሚቴው እቅድና የስራ ድርሻ ካከፋፈለ በኋላ ለተግባራዊ እንቅስቃሴ ማስታወቂያ ያወጣል፡፡ ኢትዮጵያውያንም ተካፋይ እንደሚሆኑ ማህበሩ በኢትዮጵያውያን ላይ ይተማመናል፡፡
የኢትዮጵያ ቀን 2008 ኢማኖ ኖርዌይ ውስጥ እንደ ድርጅት ከተመዘገበ 10 ዓመት ስለሚሞላው ቀኑ ይከበራል፡፡ ስለ ማህበሩ ታሪክ ባጭሩ፣ እንቅስቃሴወችና ገለጻ ይደረጋል፡፡ ይኸን ተከትሎ ፕሮጀክቶችም ይካሄዳሉ፡፡ አውደ ትዕይንት፣ ፈሊጥ፣ የተለያዩ ምግቦች ወዘተ ይኖራል፡፡ ቦታው ኦስሎ ሶፊየንበርግ ፓርክ ነው፡፡ ቅዳሜ ነሃሴ 16 ከ1200 - 2000. ዝግጅቱ ለሁሉም ክፍት ነው፡፡
የኢትዮጵያውያን የበጋ ስፖርት ፊስቲቫል፤ ፌስቲቫሉ የእግር ኳስ፣ የመረብ ኳስ፣ የጠረጴዛ ኳስና የሩጫ ውድድር ይገኝበታል፡፡ ልክ እንደ 2007 ሴትና ወንድ ከልጆች እስከ አዋቂዎች ብዙ ኢትዮጵያውያን የሚሳተፉበት ፌስቲቫል ነው፡፡ በማህበሩና በህብረተሰቡ ተወዳጅና የሚጠበቅ ፌስቲቫል ነው፡፡
የትምህርት እርዳታ፤ ለታዳጊ ወጣቶችና ወጣቶች በሳምንት ከ1-2 ጊዜ የትምህርት እርዳታ መስጠት፡፡
የባህልና ያብሮ መዋሀድ ጉባኤ፤ ቤተሰብና አብሮ መኖርን በተመለከተ እውቀትን ማስፋትና ማሳደግ፡፡
የባህልና ባህሪ ለውጥ፤ ኖርዌይ ውስጥ ለመኖር ቀለል እንዲል አስተሳሰብና ባህሪን በተመለከተ ጉባኤ ማድረግ፡፡
ስነ ጥበብና ውህደት፤ ኢትዮጵያውያን ስነ ጥበበኞች በኖርዌጅኛ እንዲጽፉ ማበረታታት፡፡
ከላይ የተጠቀሱት ስድስቱም ፕሮጀክቶች በአውሮፓውያን 2008 ላይ ተጠናቀው ለኦስሎ ኮሙና ሪፖርት ቀርቧል፡፡
ከታች አስተያየት ወይም ነጥብ ይስጡ!
This policy contains information about your privacy. By posting, you are declaring that you understand this policy:
This policy is subject to change at any time and without notice.
These terms and conditions contain rules about posting comments. By submitting a comment, you are declaring that you agree with these rules:
Failure to comply with these rules may result in being banned from submitting further comments.
These terms and conditions are subject to change at any time and without notice.
የተሰጡ አስተያየቶች