የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ በግለሰቦች ተነሳሽነት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1987 ጀምሮ ይንቀሳቀስ ነበር፡፡ ከ1998 ጀምሮ ግን በኖርዌይ ውስጥ እንደ ድርጅት ሆኖ ተመዝግቦና እውቅና አግኝቶ ይንቀሳቀሳል፡፡ ማህበሩ በየ ሶስት አመቱ ዲሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ ተወካዮች ይመርጣል፡፡ እንዚህም ተወካዮች ሶስት አመታት ያህል ማህበሩን ይመራሉ፡፡
የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ ሰላምንና ዴሞክራሲን ለሚሹ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆችን ለማስተናገድ ምንጊዜም ክፍት ነው፡፡ ወደፊትም በዚሁ መልክ ይቀጥላል፡፡ ማህበራችን ማንንም በዘር ወይም በሃይማኖት አይለይም፡፡ ስለዚህ ኢ.ማ.ኖ. የሁሉንም ኢትዮጵያውያንን ፍላጎት ለማሟላት የግለሰብ ነጻነትን ያስቀድማል፡፡
ማህበሩ ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኢትዮጵያውያን እንድሁም ስለኖርዌይና ኖርዌጅያውያን ቀና አስተሳሰብና ግንዛቤ አለው፡፡ ማህበሩ በኖርዌይ ውስጥ ተሰሚነት ኖሮት ተጽዕኖ እንዲያደርግ ኢትዮጵያውያን በሰፊው የማህበሩ ተሳታፊና አባል እንደሚሆኑ ማህበሩ በኢትዮጵያውያን ላይ ይተማመናል፡፡ የማህበሩ አንደኛውና ዋናው አላማ በኢትዮጵያውያን መካከል ስምምነትና ውህደትን የበለጠ ለማዳበር ነው፡፡ ከዚህም በማያያዝ የተለያዩ ትምህርታዊ እንቅስቃሴወችና ውይይቶች ለማድረግ እቅድ ያወጣል፡፡ ለምሳሌ፤ የኖርዌይን ባህልና ወግ እንልመድ፣ የራሳችንንም አንርሳ፣ ስለ ሙያና ስራ ማግኘት፣ ስለ ቀጠሮና ምንነት በመሳሰሉት ላይ ትምህርታዊ ውይይት ለማድረግ እቅድ ያወጣል፡፡
ማህበራችን እንዲሻሻል አንዳንድ ምቹና ምክንያታዊ ለውጦች እናደርጋለን፡፡ አዝናኝና ትምህርታዊ ምሽቶችም ይኖሩናል፡፡ ይህንን በተመለከተ ማስታወቂያዎች ቀደም ብለን እንለጥፋለን፡፡ ይኸን አላማ ለማሳካት ለማሳካት ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች እንደሚተባበሩን እንተማመናለን፡፡
➟ በግለሰቦች ተነሳሽነት ሃሳብ መነጨ።
➟ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1987 ላይ መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡
➟ 1998 ላይ በኖርዌይ ውስጥ ማህበር ሆኖ ተመዘገበ፡፡
➟ Orgnr. 984 047 355
➟ DEN ETIOPISKE FORENINGEN I NORGE
➟ ወድማማችነትና እህታማማችነት ለማጎልበት፤
➟ ኖርዌጃውያንና ሌሎች ዜጎች ጋር ወዳጅነት ለመፍጠር፤
➟ የኖርዌይን ባህልና አኗኗር ለማላመድ መረጃ ለመስጠት፤
➟ የኢትዮጵያን ታሪክ፣ ወግና፣ ባህል ለሌሎች ለማስተዋወቅ፤
➟ የኢትዮጵያውያንን በዓላት በጋራ ለማክበር፤
➟ መደበኛ አባል በመሆን፤
➟ ትምህርታዊና በዓላዊ ዝግጅቶች ላይ በመገኘት፤
➟ ስብሰባ ላይ የውሳኔ ተካፋይ በመሆን፤
➟ ምን ላግዝ ብሎ ማህበሩን በመጠየቅ፤
➟ ከተመረጡ አመራር ውስጥ በመግባት፤
➟ ማህበሩን በማስተዋወቅ፤
➟ ገንቢ ሃሳብ በመስጠት፤
ከታች አስተያየት ወይም ነጥብ ይስጡ!
This policy contains information about your privacy. By posting, you are declaring that you understand this policy:
This policy is subject to change at any time and without notice.
These terms and conditions contain rules about posting comments. By submitting a comment, you are declaring that you agree with these rules:
Failure to comply with these rules may result in being banned from submitting further comments.
These terms and conditions are subject to change at any time and without notice.
የተሰጡ አስተያየቶች