ይዘት ➞ መነሻ ➞ አላማ ➞ ማህበሩ እና በአላት ➞ መተዳደሪያ ደንብ ➞ አባል ይሁኑ ➞ መሰባሰቢያ ክለብ ➞ ስፖርትና ባህል 2024
✍ አድራሻ ethionor1@gmail.com
+47 970 02 935
Orgnr. 984047355
☝ አመታዊ ክፍያ ባንክ፤ 05401729420
ቪፕስ፤ 500424
ለአዋቂ፤ ከ200 ጀምሮ
ለህጻናት፤ 80 ክሮነር
ክፍያውን ሲፈጽሙ "medlemskontingent" የሚለውን መልዕክት ያካቱበት።
በቅድሚያ እናመሰግናለን!

ማህበሩ እና በአላት አከባበር

ecn defin ethiopia norway amharic ethiopian community

ዲስ አመት እና ሌሎች በአላትን ማህበሩ ከኢትዮጵያውያን እና ሌሎች ፍላጎት ካላቸው ዜጎች ጋር ያከብራል። እነዚህ በዓላት ሲከበሩ ልክ እንደ ኢትዮጵያ በዕለቱ ቀን ባይሆንም ቀራቢው ቅዳሜ ላይ ይከበራሉ። ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በአላትን አብረው ሲያከብሩ ማህበሩን ለማወቅ አንዱ ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡ ቤተሰቦች፣ ግለሰቦችና የሀይማኖት ተቋማት በዕለቱ ላይ እንደሚያከብሩ ይታወቃል፡፡

ለነዚህ በዓላት ዝግጅቶች ማህበሩ ቅድሚያ እንዳለው ይታወቃል፡፡ ለብዙ አመታት ሲሰራበትም ቆይቷል፡፡ ከማህበሩ ውጭ በተመሳሳይ ቀን ላይ ዝግጅት የሚያደርጉ አካላት ቀደም ብለው ማህበሩን ቢያሳውቁት መልካም ነው፡፡ ድርብ ዝግጅቶች እንዳይኖሩ ማህበሩ ከሌሎች አካላት ጋር በጋራ መፍትሄ ለማግኘት ይጥራል፡፡ ማህበሩ ቀራቢው ቅዳሜ ላይ ለማክበር የወሰነበት ምክንያት ውጭ ስለምኖር ከስራም ወይም ከትምህርት አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ነጻ የሚሆንበት ቀን ቅዳሜ ስለሆነ ነው፡፡

እነዚህ በዓላት በሰፊውና ባዝናኝ መልኩ ምቹ ሆነው እንዲከበሩ ማህበሩ የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል፡፡ ቀን ላይ የልጆችና የቤተሰቦች ዝግጅት አለ፡፡ አንዳንዶቹ እንቅስቃሴዎች የልጆች ጨዋታ፣ ውድድር፣ ሽልማት፣ የልጆች ዘፈን፣ ምግብና መጠጦች፣ የቡና ስናስርዕት የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ምሽት ላይ ደግሞ ከምግብና ከመጠጥ ጋር የሙዚቃ ምሽት አለ፡፡

ከታች አስተያየት ወይም ነጥብ ይስጡ!

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
1000
Powered by Commentics

የተሰጡ አስተያየቶች

አስተያየት ገና አልተሰጠበትም። የመጀመሪያው ይሁኑ!